info@tanamfi.com
 0583209978
☰
×

ቀን: 25/01/2019 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ  አንቀፅ 366(1)፣367(1) እና 372 መሰረት የጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሙሉዓለም የባሕል ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚያካሂድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔው እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የማኅበሩ ዓይነት የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን  ማኅበር ነው፡፡

·       የማኅበሩ የተከፈለ ካፒታል…………..104,595,000.00

·       የማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር…………….AM/BD/3/0000833/2011

·       የማኅበሩ ድረ-ገፅ…………………….www.tanamfi.com

·       የማኅበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡-………ባሕር ዳር ከተማ ፋሲሎ ክ/ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር B66 አጼ ሰርፀ ድንግል ት/ቤት ጀርባ

                 የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

1.   የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤

2.   አዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና ማጽደቅ፤  

3.   በነባር በባለአክሲዮኖች የተገዙ ተጨማሪ አክሲዮኖችን መቀበልና ማጽደቅ፤

4.   የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ክንውን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤

5.   የውጭ ኦዲተሮችን የ2025/26 ሒሳብ ዓመት  ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤

6.   ከ2019 እስከ 2021 ዓ.ም ባሉት ተካታታይ ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተር መሾም እና ክፍያቸውን መወሰን፤

7.   በ2025/26 ሒሳብ  ዓመት በተገኘው ትርፍ ክፍፍል ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤

8.   የ2025/2026 ሒሳብ ዓመት ከተገኘው ትርፍ  ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የድካም ዋጋ መወሰን፤

9.   የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፣

ማሳሰቢያ፡- በጉባዔው ለመሳተፍ ስትመጡ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንድትይዙ እና በጉባዔው መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከጉባዔው 3 ቀናት በፊት የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ባሕር ዳር ከተማ አጼ ሰርፀድንግል ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው በዋና መስሪያ ቤቱ ጽ/ቤት ወይንም በተቋሙ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት እንድትወክሉ  ወይም ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ በመያዝ በስብሰባው ላይ እንድተገኙ ጥሪውን ያስተላለፋል፡፡ 

የጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ!!

Categories and Recent News