ቀን 26/01/2018 ዓ/ም
የጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች የስብሰባ ጥሪ
በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀፅ 366፣367፣370 እና 372 መሰረት የጣና ማይክሮ ፋይናንስ
ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ
3፡00 ጀምሮ በሙሉዓለም የባሕል ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚያካሂድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ
ጉባዔው እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የማኅበሩ ዓይነት የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡
· የማኅበሩ የተከፈለ ካፒታል…………..80,770,000.00
· የማኅበሩ የተፈረመ ካፒታል………….80,770,000.00
· የማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር…………….AM/BD/3/0000833/2011
· የማኅበሩ ድረ-ገፅ…………………….www.tanamfi.com
· የማኅበሩዋና መ/ቤት አድራሻ፡-………ባሕር ዳር ከተማ ፋሲሎ ክ/ከተማ ቀበሌ
03 የቤት ቁጥር B66 አጼ ሰርፀ ድንግል ት/ቤት ጀርባ
የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
2. አዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
3. በነባር በባለአክሲዮኖች የተገዙ ተጨማሪ አክሲዮኖችን
መቀበልና ማጽደቅ፤
4. በባለአክሲዮኖች የተደረገ የአክሲዮን ዝውውርን ማጽደቅ፤
5. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2024/25 በጀት ዓመት
ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
6. የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ
ማጽደቅ፤
7. በ2024/25 በጀት ዓመት በተገኘው ትርፍ ክፍፍል
ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤
8. በ2024/25 ከተገኘዉ ትርፍ ላይ ለሥራ አመራር
ቦርድ ክፍያ ተወያይቶ መወሰን፤
9. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ
የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1. በንግድ ህጉ አንቀጽ 255 እና አንቀጽ 400 መሰረት የአክሲዮን ማህበሩን
መመስረቻ ጽሁፍ ላይ ተወያይቶ ማሻሻል፤
2.የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ
ማሳሰቢያ፡-
በጉባዔው ለመሳተፍ ስትመጡ የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንድትይዙ እና በጉባዔው መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከጉባዔው 3 ቀናት
በፊት የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ባሕር ዳር ከተማ አጼ ሰርፀድንግል ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው በዋና መስሪያ ቤቱ ጽ/ቤት ወይንም
በተቋሙ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት እንድትወክሉ ወይም ስልጣን ባለው
የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ በመያዝ በስብሰባው ላይ እንድተገኙ ጥሪውን ያስተላለፋል፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ